Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ለአርሰናል ውጤት ማጣት ሀላፊነቱን እወስዳለሁ- ሚካኤል አርቴታ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ለአርሰናል ውጤት ማጣት ሀላፊነቱን እንደሚወስድ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ገለፀ።

አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ በሰጠው መግለጫ በሀሉም መገናኛ ብዘሃን የሚቀርቡ ወቀሳዎችንም እንደሚቀበል ነው ያስታወቀው።

ትችቱ ተፈጥሯዊ ነው ያለው አሰልጣኙ የስራ አካል በመሆናቸው ትችቶችን እቀበላለሁ ብሏል፡፡

በመጨረሻው ሰዓት ውጤት ማግኘት ካልቻልክ ዋናውን ሃላፊነት የሚወስደው አሰልጣኙ በመሆኑ ምክንያት ሃላፊነቱን እንደሚወስድም ገልጿል።

“ምንም አይነት ምክንያት ማቅረብ ትችል ይሆናል ሆኖም በመጨረሻው ሰዓት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይጠበቅብሃል” ያለው አርቴታ “ያለፉት ሳምንታት ውጤቶችን መቀበል ለአርሰናል አይነት ትልቅ ክለብ ከባድ ነው” ብሏል።

አርሰናል በፈረንጆቹ ህዳር እና ታህሳስ ወር ካደረጋቸው ስድስት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ውስጥ በአራቱ ሽንፈትን አስተናግዷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version