ስፓርት

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጠች

By Abrham Fekede

December 14, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ተመረጠች፡፡

ይህንንም ተከትሎ አትሌት ደራርቱ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት  ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ትመራለች፡፡

ከዚህ ቀደም ላለፉት ሁለት ዓመታት  የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን በማገልገል ላይ ነበረች፡፡

አትሌቷ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሆና የተመረጠችው በ27 የድጋፍ ድምጽና በአንድ የተቃውሞ ድምጽ መሆኑን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!