አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል እየተካሄደ የሚገኘው የሽግግር ሂደት በክልሉ የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር መሰረት የሚጥል መሆኑን የጊዜያዊ አስተደዳሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ተናገሩ።
በሽግግር ሂደቱ ህዝቡ ጊዜያዊ አስተዳዳሪዎቹን እየመረጠ በጥሩ መልኩ በመከናወን ላይ መሆኑንም ዶክተር ሙሉ ገልጸዋል።
የህወሓት ቡድን የክልሉን ህዝብ በአንድ ለአምስት በማደራጀትና ፖለቲካዊ ጫና በማሳደር አፍኖት መቆየቱን አስታውሰው÷አሁን ነፃነቱን አግኝቷል ብለዋል።
በመሆኑም በክልሉ እየተካሄደ የሚገኘው የሽግግር ሂደት የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር መሰረት የሚጥል መሆኑን አስረድተዋል።
የጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራ አስፈጻሚ ህዝቡ በቀጥታ በመረጠው አስተዳደር እና መሪ እንዲተዳዳር እያመቻቸ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በዚህ ሂደት የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችም የበኩላቸውን ድርሻ በመወጣት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የህወሓት ጁንታ ሲጠቀምበት የነበረው ሚዲያ ለህዝብ ትክክለኛ መረጃ እንዲያደርስ ለማስቻል በሂደት ላይ መሆኑንም ዶክተር ሙሉ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡