አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የሊቨርፑል አሰልጣኝ ጄራርድ ሁዬ በ73 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ጄራርድ ሁዬ ሊቨርፑልን ከፈረንጆቹ 1998 እስከ 2004 ድረስ በአሰልጣኝነት መርተውታል።
በሊቨርፑል በነበራቸው ቆይታም የኤፍ ኤ ካፕ፣ የሊግ እና በቀድሞው ስያሜው የአውሮፓ ማህበረሰብ ዋንጫ በአሁን መጠሪያው ዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ አምስት ዋንጫዎችን ከቡድኑ ጋር አንስተዋል።
ጄራርድ ሁዬ ከሊቨርፑል ባሻገር ሌንስ፣ ፓሪስ ሴንትጀርመን፣ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን እና ሊዮንን በአሰልጣኝነት መርተዋል።
በመጨረሻ አስተን ቪላን በአሰልጣኝነት የመሩ ሲሆን ሲሆን በ2011 ከልብ ህመም ጋር ተያይዞ ከዘጠኝ ወራት በኋላ ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።
ሊቨርፑል ባወጣው የሀዘን መግለጫ በቀድሞ አሰልጣኝ ጄራርድ ሁዬ ህልፈት በጥልቁ አዝነናል ብሏል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!