Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ኮቲዲቯር ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ኮቲዲቯር ገቡ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በኮትዲቯሩ ፕሬዚዳንት አላሳኔ ኦታራ በአለ ሲመት ላይ ለመገኘት ነው ወደ ስፍራው ያመሩት፡፡

ፕሬዚዳንቷ አቢጃን ሲደርሱ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀማድ ባካዮኮ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በኮትዲቯር ቆይታቸው ከተለያዩ ሃገራት መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፕሬዚዳንት ፅጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version