Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢንዶኔዥያ መዲና በጎርፍ አደጋ የ21 ሰዎች ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2012(ኤፍቢሲ) በኢንዶኔዥያ መዲና ጃካርታ በጎርፍ አደጋ 21 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ።

አውሎ ነፋስ በቀላቀለው ከባድ ዝናብ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ አዲስ አመትን ለመቀበል አደባባይ በወጡ ዜጎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

ከባድ ዝናብ እና የወንዞች የውሃ መጠን መጨመር ለጎርፍ አደጋው መባባስ ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው።

በጎርፍ አደጋው ሳቢያ የሃገር ውስጥ በረራ የሚሰጠው አውሮፕላን ማረፊያ ሲዘጋ፥ 20 ሺህ መንገደኞችን ከጉዞ ተስተጓጉለዋል ተብሏል።

ከጃካርታ ወጣ ብላ በምትገኝ አካባቢም በጎርፉ ሳቢያ የመሬት መንሸራተት አደጋ ማድረሱም ተነግሯል።

አሁን በመዲናዋ የጣለው የዝናብ መጠን ከአመታዊ የዝናብ መጠን በሶስት እጥፍ የበለጠ ነው።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

Exit mobile version