አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የለገጣፎ ለገዳዲ አትሌቲክስ ማዘውተሪያን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የለገጣፎ ለገዳዲ የአትሌቲክስ የአሸዋ ትራክን ነው በዛሬው እለት መርቀው በይፋ ስራ ያስጀመሩት።
በምረቃው ላይ አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እና የለገጣፎ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ተገኝተዋል፡፡