Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጀርመን በሳዑዲ ላይ ጥላው የነበረውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ ለአንድ አመት አራዘመች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጀርመን በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ ጥላው የነበረውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ ለአንድ አመት አራዘመች፡፡

ማዕቀቡ የተራዘመውም ሪያድ በአሁኑ ወቅት በየመን የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ በምታደርገው ጣልቃ ገብነት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

በዚህ መሰረትም በርሊን እስከ የሚቀጥለው ዓመት ድረስ ለሪያድ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ሽያጭ እንደማታከናውን የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡

ጀርመን በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2018 ላይ ከጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ ጋር በተያያዘ ነበር በሳዑዲ ዓረቢያ ላይ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማዕቀብ የጣለችባት፡፡
ምንጭ፡-ሚድል ኢስት ሞኒተር

Exit mobile version