Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በጋምቤላ ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት የተከማቹ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋምቤላ ከተማ በአንድ ግለሰብ ቤት ተከማችተው የተገኙ 199 የተለያዩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ጸጥታ አካላት አስታወቁ ።

በክልሉና ፌዴራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት  አገልገሎት  የተቀናጀ ጥረት በቁጥጥር ስር  የዋሉት ህገ ወጥ  መሳሪዎች  148 ታጣፊ  እና 51 ባለሰደፍ  ክላሺንኮቭ   ጠብንጃዎች በተጨማሪም 178  የጥይት መያዣ  ካርታዎች እንደሚገኙበት ተመልክቷል።

የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ  ቶማስ ቱት እንዳሉት ክልሉ  ከደቡብ ሱዳን ጋር  ሰፊ የድንበር ወሰን ያለው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይገባል።

የክልሉ ፖሊስ  ኮሚሽነር ኮማንደር ኡማን ኡጋላ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ከህዝብ የደረሳቸውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ በተደረገ የተጠናከረ ክትትል ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ተከማችተው የተገኘበትን ቤት ባለቤት ጨምሮ አዘዋዋሪዎችንና ሌሎች ግብር አበሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ የተገኙት ከአንድ ሳምንት በላይ በተደረገ ክትትል  መሆኑን  የገለጹት ደግሞ ኦፕሬሽኑን የመሩት የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር  ናቸው።

ኮሚሽኑ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የቡድን ጨምሮ ሌሎችም በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ህገ ወጥ  የጦር መሳሪያዎች መኖራቸውን ጠቁመው መሳሪያዎቹን ቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

Exit mobile version