Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአዲስ አበባ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ላደረጉ አካላት የእውቅና እና የምስጋና መርሐግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ለመከላከያ ሰራዊቱ በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ ላደረጉ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የእውቅና እና የምስጋና መርሐግብር ተካሂዷል።
በማጠቃለያ እውቅና እና የምስጋና መርሐግብሩ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጨምሮ የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነአ ያደታ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጀነራል ብርሃኑ ጁላ፣ሚኒስትሮች እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እእንዲሁም ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ህዝቡ በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በህውሓት ጁንታ ቡድን የደረሰበትን ጥቃት ከማውገዝ ጀምሮ በሞራል፣ በደም ልገሳ ፣በገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ በማድረግ ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብር አሳይተዋል በማሳየት ላይም ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም መላው ነዋሪዎች እና ልዩልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመከላከያ ሰራዊቱ ያደረጉትን ገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ለማመስገን እና እውቅና ለመስጠት ነው የማጠቃለያ መርሃ ግብሩን አዘጋጅቷል።
በዚሁ ወቅት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ÷ የከተማዋ ነዋሪዎች የህውኃት ጁንታ ቡድን በሰሜን ዕዝ በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው አስነዋሪ ድርጊት ከማውገዝ ጀምሮ በሞራል፣በደም ልገሳ ፣በገንዘብ እና በአይነት ላበረከቱት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
አያይዘውም በዚህ ድጋፍ የታየው አብሮነት በመስጠት ብቻ አላበቃም ያሉት ወይዘሮ አዳነች ህግን በማስከበር ላይ ለተሰማራው ሠራዊታችን ትልቅ እገዛ ነው ብለዋል።
የከተማዋን አስተማማኝ ሰላም በማረጋገጥ ሌት ተቀን ለሠሩ የፀጥታ ሃይሎች ፣የህዝብ አደረጃጀቶች እና መላው ነዋሪዎች ምክትል ከንታባዋ ምሥጋና ማቅረባቸውን ከአስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version