Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ያልተነገረ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ገድል

ምክትል ኮማንደር ቢራራ ተባባል ዓለማየሁ ይባላል፤ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሰሜን ዳይሬክቶሬት የዲቪዥን 2 አባል ናቸው።

መኮንኑ ከህዳሴ ዲቪዥን በጋንታ አመራርነት አድገው ወደ መቐለና ሰሜን ጎንደር የሚሄዱ 39 የሚሆኑ የዲቪዝኑን አባላት ጭነው ጉዞ ለመጀመር ይዘጋጃሉ።

ከእንቅስቃሴው በፊት የጁንታው ቡድን ተላላኪዎች እስረኛ ለማስለቀቅ ማንኩሽ የተባለ ስፍራ ተኩስ ከፍተው ስለነበር አሁንም ተልዕኮ ተቀብለው ትንኮሳ ሊፈፅሙ እንደሚችሉ በመገመት አባላቱን በሁለት ቡድን በመክፈልና ከመሃከላቸው አመራር የሚሰጡ ሁለት አባላት በመመደብ ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ጉዞ ይጀመራሉ።

መኮንኑ እንደሚሉት ጉብላትና ማንቡክ መካከል ቁጥር 3 የተባለ ስፍራ ሲደርሱ የጁንታው ህወሃት ቡድን ተላላኪዎች በመከላከያ ታጅበው በሚሄዱ ከ100 በላይ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ቁሳቁስ የጫኑ የሳሊኒ ተሽከርካሪዎች ላይ ተኩስ በመክፈት አስገድደው ንብረቱ እንዳይደርስ ለማስቆም ሲሞክሩ ያገኙዋቸዋል።

ምክትል ኮማንደሩ ቀደም ሲልም ተኩስ ተከፍቶባቸው ተታኩሰው ማለፋቸውን ገልፀው፤ የጁንታው ቡድን ጀሌዎች ዓላማ ለግድቡ የሚቀርበውን ቁሳቁስ የጫኑትን መኪኖች ለማስቆም መሆኑን ስለተረዱ በእጀባ ላይ ከነበሩት ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመተባበር አባላቱን ይዘው ተኩሱን መቀላቀላቸውንና ከቀኑ 7 ሠዓት እስከ ምሽቱ 1 ሠዓት ሲታኮሱ መቆየታቸውን የተናገሩት መኮንኑ የጁንታው ቡድን ተላላኪዎች ሽፋን ሰጪ ከባድ መሳሪያ ሲጠቀሙ እንደነበርም ጠቁመዋል።

ከዚህ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ በኋላ የጁንታውን ተላላኪዎች አንገት አስደፍተው ተሽከርካሪዎቹን ማሳለፋቸውን የገለፁት መኮንኑ ተረባርበው ተሽከርካሪውን ባያስወጡ ኖሮ የከፋ ጉዳት ይደርስ እንደነበር ተናግረዋል።

ምክትል ኮማንደር ቢራራ ተባባል አስተባባሪነት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በእጀባ ስራ ላይ ከነበሩት ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ድል በማድረግ የጁንታው ታላላኪዎችን አንገት ያስደፋ የጀብዱ ተግባር ፈጽመዋል።

በመጨረሻም በማግስቱ በተደረገ ማጣራት ከ23 በላይ የጁንታው ተላላኪዎች መደምሰሳቸውንና አካባቢው ሠላም መሆኑን አረጋግጠው ጉዞዋቸውን መቀጠላቸውን ምክትል ኮማንደር ቢራራ ተባባል መናገራቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version