አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የንግድናኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከአለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አስተባባሪ በሆኑት በቼክ ኦማር ሲላ ከተመራ ልኡክ ጋር ተወያዩ።
የገንዘብ ድጋፍ ብቻውን የአንድን ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት እውን ሊያደርግ አይችልም ያሉት ሚኒስትሩ÷ አይኤፍሲ እያደረገ ያለው ድጋፍና በቀጣይም ሀገራችን እያካሄደች ያለችውን ለውጥ ከግብ ለማድረስ ከመንግስት ጎን ያለውን ቁርጠኛ የድጋፍ አጋርነት በመግለጹ አድንቀዋል።
አቶ መላኩ አያይዘውም ኢትዮጵያ የእምቅ ሀብት ባለቤት ናት ፣ ያለንን እምቅ ሀብትና አቅም ተጠቅመን የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ዕውን ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት በእውቀት፣ በካፒታል፣ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ የስራ አተገባበርና በሌሎች ዘርፎች ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
የአለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን የምስራቅ አፍሪካ አስተባባሪ ቼክ ኦማር ሲላ በበኩላቸው÷ ተቋማቸው በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ እውን ለማድግ አስፈላጊና ቁልፍ የሚባሉ ዘርፎችን በገንዘብ፣ በትምህርትና ስልጠና፣ በአቅም ግንባታ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊነትና ሌሎች ዘርፎችን ድጋፍ በማድግ ለለውጡ እውን መሆን በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!