Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የወጣቶችና የአፍላ ወጣቶች ጤና ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወጣቶችና የአፍላ ወጣቶች ጤና ትኩት ተሰጥቶት መሰራት እንደሚገባና የሚመለከታቸዉ አካላት ሚናቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ ተገለፀ።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ እንደገለጹት÷ የአምስት ዓመቱ የጤና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ብዙ ዉይይት የተደረገበት እንደሆነና የወጣቶችና የአፍላ ወጣቶች ጤና በዚህ ዕቅድ ዉስጥ ተካተዉ ከሚተገበሩ የጤና ዕቅዶች መካከል አንዱና ዋናዉ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ መስራትም ከጤናዉ ባለፈ በሀገር ደረጃ የራሱ የሆነ ጠቀሜታ እንዳለዉ ተናግረዋል፡፡
በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት ዳይክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በበኩላቸው ÷የወጣቶችና የአፍላ ወጣቶች ጤና በጤና ሚኒስቴር ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንዳለ ተናግረዋል፡፡
ከሚታየዉ ችግር ሰፊነት አንጻርም የሚመለከታቸዉ አካላት በተበታተነ ሁኔታ የሚያከናዉኑትን ተግባራት በአንድ ማዕከል በማድረግ የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል መግለፃቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version