Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠ/ሚ ዐቢይ እና ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላሙን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላሙ ግዛትን ጎበኙ።

ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኬንያ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ጋር በመሆን የሞምባሳ-ናይሮቢ -አዲስ አበባ- ኮሪደር ግንባታ አካል የሆነው የሀዋሳ ሞያሌ መንገድ እና የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ፕሮጀክት መርቀው መክፈታቸው የሚታወስ ነው።

በማርሳቢት ሞያሌ የነበራቸውን ቆይታ ያጠናቀቁት መሪዎቹ ላሙ ግዛት ገብተዋል።

በግዛቱ በነበራቸው ቆይታ የላሙ ወደብ ግንባታ ሂደትን መጎብኘታቸው ተነግሯል።

የላሙ ወደብ የመርከቦች ማቆያ የላፕሴት ኮሪደር ፕሮጄክት አካል ነው።

መሪዎቹ በግዛቱ ባደረጉት ጉብኝት የኬንያ ተቃዋሚ መሪ ሪይላ ኦዲንጋ መገኘታቸው  ተጠቁሟል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version