አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በ25 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ ሜዳ ግንባታን አስጀመረ፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የሚገኘው የፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ ሜዳ ግንባታን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን እና የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ተክሌ በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል።
ለአጠቃላይ የሜዳው ግንባታ ከ25 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘለት ሲሆን በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን ገልጸዋል፡፡
የፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ ሜዳ ግንባታ ለረጅም ዓመታት የወጣቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን የገለጹት ኮሚሽነር በላይ የሜዳው ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት እስኪበቃ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቡ ፕሮጀክቱን ሊደግፉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሜዳው ደረጃውን የጠበቀ የእግር ኳስ ሜዳ፣ ሁለት የፉትሳል መጫወቻ ሜዳ፣ የመሮጫ ትራክ፣ የተመልካች መቀመጫ፣ ዙሪያ የሽቦ አጥር፣ ሻወር ቤት፣ የቲኬት ቢሮ እና የልብስ መቀየሪያ ክፍሎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡
ግንባታውን በተቀመጠለት ጊዜ እና ፍጥነት ለማጠናቀቅ በሙሉ አቅም እንደሚሰራ የውብኮን ስራ ተቋራጭ እና ዘውዱ ተስፋዬ ኮንሰልታንሲ ተወካዮች መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!