አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካናዳ ኦታዋ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ኢትዮ-ካናዳውያን ኔትዎርክ ፎር አድቮኬሲ ኤንድ ሰፖርት ፣ በካናዳ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች ማህበር እና የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች በድጋፍ ማሰባሰብና አቅርቦት ላይ ውይይት አካሄዱ።
በውይይቱ በካናዳ ኦታዋ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊን ጨምሮ የተቋማቱ ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ኤምባሲው የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትዎርክ ፎር አድቮኬሲ ኤንድ ሰፖርትን የማስተባበር ስራ ሰርቷል።
በአገራችን ህግ ማስከበር ላይ ለሚገኘው የመከላከያ አባላትና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አገልግሎት የሚውሉ የህክምና ቁሳቁስ እና መድሃኒቶችን በተቻለ ፍጥነት በማሰባሰብ ለማድረስ ተመክሯል።
እንዲሁም ቀጣይነት ባለው መልኩ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የህክምና ተቋማት ሙያዊና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄዷል፡፡
በዚሁ መሠረት እስከአሁን የተገኙ የህክምና ቁሳቁሶች በሀገር ውስጥ ወደሚፈለግበት ቦታ በፍጥነት ለማድረስ መከናወን በሚገባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ተደርሷል።
ቀጣይ መሰል ድጋፎችን ለማሰባሰብ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚያስፈልጉና አስቀድመው መታወቅ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ከሁሉም ወገን ሃሳቦች ቀርበው በመወያየት መግባባት ላይ መደረሱን በካናዳ የኦታዋ ኤምባሲ ገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!