የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርዓት የወደፊት ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ የተቋቋመውን ኮሚሽን ሰበሰቡ

By Abrham Fekede

December 07, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓለም ዓቀፉ የትምህርት ስርዓት የወደፊት ሁኔታ ላይ ለመምከርና ለማቀድ የተቋቋመውን ኮሚሽን ሰበሰቡ፡፡

ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምሁራንንና ባለሙያዎችን ያቀፈው ኮሚሽኑ ለወደፊት ዘመናዊ እና ሁሉን ዓቀፍ ትምህርት ምን መምሰል እንዳለበት ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለመምህራንና ለተማሪዎች መመሪያ ሆኖ የሚያገለግል ሪፖርት እያዘጋጀ መሆኑን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገነነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኮሚሽኑ አባላት እስካሁን በተሰራው ስራ ላይ ተወያዩ ሲሆን ሪፖርቱን በፈረንጆቹ በ2021 መጨረሻ እንደሚታተም ነው የተገለጸው፡፡

ኮሚሽኑ በ2019 በኒውዮርክ በተዘጋጀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መመስረቱ ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን