አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲዎች ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት መካሄዱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በስራ ላይ የሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ፕሮግራም በ1986 ዓ.ም የተዘጋጀ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ መሆኑን በውይይቱ ላይ አንስተዋል፡፡
ፖሊሲው ያሳካቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆኖ እንዴት አድርገን ሁለንተናዊ የሀገሪቱን ብልጽግና እናሳካለን ለሚለው ብዙ ጥናቶች መደረጋቸውንም አንስተዋል፡፡
ጥናቱን ተከትሎ የሀገሪቱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መዘጋጀቱንም ጠቅሰዋል፡፡
በሪፎርሙ የግብርና፣ ማምረቻው ዘርፍ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ቱሪዝምን ማዕከል ያደረጉ ብቁ ምሩቃንን በማፍራት ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር በማድረግ የኢኮኖሚ ስብራቱና የምርታማነት ማነስ የሚቀርፍ ስልት ያካተተ ስትራቴጂክ ዕቅድ መሆን ይጠቅበታልም ነው ያሉት፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማህበረሰብ አገልግሎትን በማስፋት፣ ሰውን ምሉዕ አድርጎ ማውጣት የሀሳብና የእውቀት መፍለቂያ በመሆን የዲፕሎማሲ አቅምን የሚጨምሩ መሆን እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል፡፡
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት 21 ቁልፍ የፖሊሲ ጉዳዮች የያዘ ሰነድ እና 6 ፕሮግራሞች መነሻ ሠነዶች መቀረጻቸውም በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡
በውይይቱ ላይ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያቀርቡት ዕቅድ መማማሪያ መሆን እንደሚጠበቅበትና በዘርፎቹ ጠቃሚ የሆነ የተሻለ ዕቅድ ላቀረበ ዩኒቨርሲቲ እውቅና እየተሰጠ መሻሻል ያለበት ዕቅድ ማሻሻያ እየታከለበት እንደሚዳብርም ነው የተገለጸው፡፡
በውይይት መድረኩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የበላይ አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መሳተፋቸውን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን