የሀገር ውስጥ ዜና

በህግ ማስከበር ሂደት ወቅት ሰግተው ከአላማጣ ወደ ቆቦ ተሻግረው የነበሩ ወገኖች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል

By Tibebu Kebede

December 06, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህግ ማስከበር ሂደት ወቅት ሰግተው ከአላማጣ ወደ ቆቦ ተሻግረው የነበሩ ወገኖች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል።

የሰላም ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋሙ ብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ባልደረቦች በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተለያዩ አካባቢዎች በአካል በመገኘት የዕለት ደራሽ ሰብዓዊ ድጋፍና ወገኖችን መልሶ የማቋቋም ተግባራትን በማስተባበር ላይ ይገኛሉ።

የሰላም ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአላማጣ፣ ጨርጨር፣ መኾኒ፣ እንዲሁም ኮረም አካባቢዎች እንደተሰጋው ተፈናቃይ ባይኖርም በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ለመደገፍ በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አቀናጅነት የእናቶችና ዕፃናት አልሚ ምግብን ጨምሮ የዕለት ደራሽ እርዳታ የማሰራጨት ስራ እየተሰራ ነው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!