አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የደረሱ ሰብሎችን ሰበሰቡ፡፡
ከፌዴራል እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጡ የፖሊስ አባላት እና በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አጋዥ እና አቅም የሌላቸው የአርሶአደሮች ሰብልን የመሰብሰብ ስራ አከናውነዋል ።
በሰብል መሰብሰብ ስራ የተሳተፉ የፖሊስ አባላት÷ለሀገራችን ሰላምና ፀጥታ ዘብ ከመቆም በሻገር በተለያዩ የማህብረሰብ አቀፍ የልማትና የበጎ ፍቃድ ተግባራት ላይ በንቃት በመሳተፍ የህዝብ አለኝታነታችንን በተግባር እናረጋግጣለን ሲሉ ገልጸዋል ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፈቲያ መሀመድ ÷ በሰብል መሰብሰብ መርሀግብር ላይ የተሳተፉ የፀጥታ አካላትን እና ወጣቶች ላደረጉት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል ።
የተጀመረውን የአቅመ ደካማ አርሶአደሮች የደረሱ ሰብሎች የመሰብሰብ እና ሌሎች መሰል የበጎ ፍቃድ ተግባራት በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ ሊቀጥሉ እንደሚገባ ስራ አስፈጻሚዋ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!