አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ቤራፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡
የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ነገ የሚካሄድ ሲሆን፥ ፕሬዚዳንቱም አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የማህበሩ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ተገኝተው ሀገሪቷ ያላትን ታላቅ የኦሊምፒክ ታሪክ ለማክበር በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ መግለጻቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በትናንትናው እለት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!