Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ ጋር ተወያዩ፡፡

በስልክ ባካሄዱት ውይይት አቶ ደመቀ መኮንን በትግራይ ክልል ስላለው የህግ ማስከበርና መልሶ ማቋቋም ስራ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የህግ ማስከበር ስራው መጠናቀቁን እና መንግስት በመልሶ ማቋቋም ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡

በመልሶ ማቋቋሙ ከህጋዊ የክልሉ መንግስት ጋር በምክክር እየተሰራ እንዳለ ገልፀል፡፡

በተጨማሪም ወንጀለኞችን በማደን ለህግ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

ዓለም አማቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ከፌደራል መንግስት ጋር በቅርበት እየሰሩ በመሆናቸውም አመስግነዋል፡፡

የዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄፔ ኮፎድ በበኩላቸው መንግስታቸው የኢትዮጵያ መንግስት መልሶ ማቋቋም እና ሰብዓዊ ድጋፍ ስራ ላይ የሚያካሂደውን ጥረት እንደሚደግፍ ገልፀዋል፡፡

ሀገራቸው ኢትዮጵያ በምታካሂደው ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version