የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በደቡባዊ ምእራብ ሶማሊያ ያስገነባቸውን የልማት ስራዎች ለአከባቢው አስተዳደር አስረክበ

By Feven Bishaw

December 04, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሊያ የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ አሚሶም አካል የሆነው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በደቡባዊ ምእራብ ሶማሊያ በባይደዋ አካባቢ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ለአካባቢው አስተዳደር አስረከበ፡፡

ፕሮጀክቶቹ ሆስፒታል እና በፀኃይ ኃይል የሚሰሩ የውሃ ፓምፖች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሆስቲታሉ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያገለግላል ነው የተባለው፡፡

ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት ከጣሊያን መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን÷ የአካባቢው ህብረተሰብ አግልገሎቱን በቅርብ ርቀት እንዲያገኝ ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል።

ርክክቡ በተደረገበት ወቅትም የአሚሶም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!