አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ 22ኛ ንስር ክፍለጦር የ3ኛ ብርጌድ 3ኛ ሻለቃ እና የፌደራል ፖሊስ አመራር ፣ ከሱዳን 13ኛ ክፍለጦር 14ኛ ብርጌድ 9ኛ ሻለቃ አመራር የጋራ ጥምር ወታደራዊ ኮሚቴ በሁለቱ ሃገራት ድንበር አካባቢ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ መሰረት ያደረገ ውይይት አካሂዷል ።
የ3ኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ሻለቃ ሰለሞን አፈራ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፤ የኢትዮ ሱዳን ግንኙነት ለበርካታ አመታት የቆየና የሁለቱ ሃገራት የትብብር ስምምነት ለሰላም ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል ።
በቀጣይነትም ሁለቱ ሀገራት በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ አመላክተዋል ።
በሱዳን የ9ኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል መሀመድ አደም ኢትዮጵያ እና ሱዳን በሰላምና ደህንነት ዙሪያ በጋራ እየሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል ።
ሁለቱ ሃገራት የመረጃ ልውውጥ በማድረግ፣ በድንበር አካባቢ የጋራ ቅኝት ስራዎች በማከናወን፣ ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውርን እና ኮንትሮባንድ ንግድን መቆጣጠር የሚያስችሉ የጋራ ስራዎች ማከናወናቸውንም ተናግረዋል ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን