አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትና የፌደራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መረጃዎችን በፋና ቴሌቪዥን ለማድረስ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትና ኤጀንሲው መሬት እና መሬት ነክ ንብረቶች ጋር ተያይዞ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ባለፉት ስድስት ዓመታት በሬዲዮ ዘርፍ በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል።
ስምምነቱ መሬት እና መሬት ነክ ንብረቶችን በተመለከተ በቴሌቪዥን መረጃዎቹን በማድረስ ስራዎቹን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርስ ነው የተጠቆመው።
በከተሞች ትክክለኛ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ እንዲኖር ስምምነቱ የራሱ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ተነግሯል።
በተለይም ከመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ጋር ተያይዞ ያለውን ሙስና ለመቀነስ፣ ለባለሀብቶች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና የመሬት ምዝገባ ለማሻሻል መሰል ዝግጅቶች የጎላ ሚና እንዳላቸው ነው የተነገረው።
በህጋዊ ካዳስተር የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ማለትም በአዋጆች፣ በመመሪያዎች፣ ማኑዋሎችና ስታንዳርዶች ላይ በቂ ግንዛቤ መፍጠር ያስችላል ተብሏል።
በከተሞች በመሬት ዘርፉ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመፍታት እና ህጋዊ ካዳስተር የህግ ማዕቀፎችን ተፈፃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!