አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጣልያን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በማድረግ በክልሎች መካከል የሚደረግ የገና ጉዞን አገደች፡፡
አውሮፓ ለገና እና አዲሱን ዓመት ለመቀበል ሽር ጉድ እያለች ትገኛለች፡፡
ይህን ተከትሎም የኮሮና ቫይረስ እንዳይስፋፋ የተለያዩ ሃገራት ክልከላዎችን እያሳለፉ ነው፡፡
ከእነዚህም መካከል ጣልያን አንዷ ስትሆን ከታህሳስ 12 እስከ ታህሳስ 27 የሚቆይ የጎዞ ክልከላ አሳልፋለች፡፡
ጣልያን ይህንን ክልከላ ያስተላለፈችው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 993 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተከትሎ ነው፡፡
ይህም ወረርሽኙ በሀገሪቱ ከተከሰተ በኋላ በአንድ ቀን የተመዘገበ ትልቅ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ክልከላውን አስመልከቶ በሰጡት አስተያየት በታህሳስ ወር ሊከሰት የሚችለውን ሦስተኛ ዙር ወይንም ሰርድ ዌቭ መከላከል አለብን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ጣልያን አሁን ይፋ ባደረገችው ክልከላ ለስራ እና ለህክምና ጉዳዮች ጉዞ መፍቀዷን ገልጻለች፡፡
ወረርሽኙ ከተከሰተበት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በሀገሪቱ ከ58 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!