Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጎግል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን የ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ተመራማሪ በማሰናበቱ በሰራተኞቹ ተቃውሞ ቀረበበት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል ትውልደ ኢትዮጵያዊቷን የ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ተመራማሪ ዶክተር ትምኒት ገብሩን በማሰናበቱ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ የተቋሙ ሰራተኞች እርምጃውን በመቃወም ግልፅ ደብዳቤ መፃፋቸው ተነገረ።

ትምኒት ገብሩ በጎግል የ”አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ስነ ምግባር ጥናት እና የሰዎችን ማንነት በፊታቸው የሚለየው ቴክኖሎጂ በአተገባበሩ ላይ ያለውን የዘር መድሎ በማጋለጧ ትታወቃለች።

ከጎግል እስከተሰናበተችበት ጊዜ ድረስ ትምኒት ገብሩ የተቋሙን “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ” ስነ ምግባር ቡድን አባል ነበረች።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ትምኒት ባዘጋጀችው የጥናት ወረቀት እና ጎግል ሰራተኞችን በተለይ ከፆታ እና ከቀለም ጋር ተያይዞ የሚያስተናግድበትን መንገድ በተመለከተ ለባልደረቦቿ ያላትን ፍርሃት ከገለፀች በኋላ ተቋሙን እንድትለቅ እንደተገደደች ተናግራለች።

ጎግል ዶክተር ትምኒት ካበረከተችው አስተዋፅኦ እና ካላት ልምድ አንፃር ሊንከባከበት ሲገባ የዘር መድሎ፣ ጥናቷን ሳንሱር በማድረግ ብሎም ከስራ እድትሰናበት አድርጓታል ሲሉ ሰራተኞች በፃፉት ደብዳቤ ላይ መግለጻቸውን ኤን ፒ አር በዘገባው ላይ አስፍሯል።

ትምኒት ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመሆን ያዘጋጀችው ጥናት ጎግልን ጨምሮ ሌሎች የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚጠቀሟቸው “አርቴፊሻል ኢንተለጀንሶች” በስነ ምግባር እና በአካባቢ ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ የሚያመለክት መሆኑ ተጠቁሟል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በዘርፉ ካሉ ውስን ጥቁር ሴት ባለሙያዎች መካከል አንደኛዋ ናት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version