አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ጸጥታና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት አመራርና አባላት የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄዱ።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ጸጥታና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት ለሀገር ህልውና ሲሉ መስዋትነት ለከፈሉ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ክብር በመግለጽ ከ600 በላይ የሚሆኑ አመራሮችና አባላት ደም ለግሰዋል፡፡
የጸጥታና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬቱ የህወሓት ጽንፈኛ ቡድን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንዲቀርቡ በሚደረገው ጥረት የፖሊሳዊ ግዴታቸውን ከመወጣት ጎን ለጎን ደም ከመለገስ ጀምሮ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!