አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮችና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎውኩክ ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱ የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ በሚሆንበት አግባብ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር ተብሏል፡፡፡
እንዲሁም በትግራይ ክልል ያሉ መሰረተ ልማቶች ወደ አገልግሎት መግባት በሚችሉበት አግባብ ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክዕተኛ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም በትግራይ ክልል በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር በሚገኙና በአማራና በአፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሰብዓዊ እርዳታን በተገቢው መልኩ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ስምምነትም በዚህ ወቅት ተደርሷል፡፡