የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከእስራኤል የዳያስፖራ ኢሚግሬሽንና የትብብር ሚኒስትር ታማኖ ሺታ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

December 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከእስራኤል የዳያስፖራ ኢሚግሬሽንና የትብብር ሚኒስትር ታማኖ ሺታ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅትም ሚኒስትር ታማኖ ሺታ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ መግለፃቸውን የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ እና በእስራኤል መካከል መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ለማጠናክር እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

የእስራኤል የዳያስፖራ ኢሚግሬሽንና የትብብር ሚኒስትር ታማኖ ሺታ ባሳለፍነው እሁድ ነበር በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት።

በእስራኤል ትውልደ ኢትዮጵያዊ እንደዚህ ያለ የስልጣን እርከን ሲይዝ የመጀመሪያ ነው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!