Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመቐለ ከተማ በተደረገ ብርበራ የጥፋት ቡድኑ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ ተይዟል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቐለ ከተማ የጥፋት ሃይሉን አባላትና የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል የቤት ለቤት ፍተሻ ተጀምሯል፡፡

በዚህም በከተማው የጥፋት ቡድኑ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ዴፖ በብርበራ በሰራዊቱ ተይዟል፡፡

በወቅቱም ሶስት ኮንቴነር ጠመንጃ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ ጥይቶች፣ ክላሽንኮብ መሳሪያ፣ ስናይፐር፣ አድማ መበተኛ የጭስ ቦምብ እና ፈንጅዎች ተይዘዋል፡፡

በተጨማሪም የትግራይ ልዩ ሃይል መለዮና የአባላት መታወቂያዎች መያዛቸውም ታውቋል፡፡

ሰራዊቱ አሁን ላይ በሚያካሂደው የፍተሻና ብርበራ የጥፋት ሀይሉ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ በርካታ የጦር መሳሪያዎች እንደሚያገኝም ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡

ለዚህም የትግራይ ህዝብ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

በተያያዘ ዜና ከቀናት በፊት በመከላከያ ሰራዊቱ ቁጥጥር ስር በዋለችው መቐለ ከተማ በተወሰነ መልኩም ቢሆን የሰዎች እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

ተዘግተው የቆዩ ሱቆችም በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች መከፈታቸውን በስፍራው የሚገኘው ባልደረባችን ባደረገው ቅኝት መታዘብ ችሏል፡፡

አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች “የምንፈልገው ሰላም ነው፤ የተቋረጡ የመብራትና የስልክ አገልግሎት ይመለሱልን” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

አሁን ላይም ሰራዊቱ ከህግ ማስከበር ዘመቻው ውጭ ምንም አይነት ተፅዕኖ እንዳልፈጠረባቸውም ተናግረዋል፡፡

በፋሲካው ታደሰ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version