Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ወንጀል የተከሰሱት ጥላሁን ያሚን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክር መሰማት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል ወንጀል የተከሰሱት ጥላሁን ያሚን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ላይ የዐቃቤ ህግ ምስክር መሰማት ተጀመረ፡፡

በዛሬው ዕለት ዐቃቤ ህግ 12 ምስክሮችን ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የሦስቱ ተሰምቷል፡፡

በተጨማሪም ሌላ አንድ ምስክር የቀረበ ቢሆንም ተመሳሳይ የምስክርነት ቃል የሚያሰማ ነው በሚል ዐቃቤ ህግ ምስክሩን ሳያሰማ ቀርቷል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀሪ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት በይደር ለነገ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version