Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ የሚካሄድበትን መሠረት ለመጣል በቁርጠኝነት መሥራቱን እንደሚቀጥል ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርጫ 2013 ቁልፍ የሽግግር ምዕራፍ በሚል በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፌደራል መንግሥት በኢትዮጵያ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ የሚካሄድበትን መሠረት ለመጣል በቁርጠኝነት መሥራቱን እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ እናተዓማኒ እንዲሆን ከዜጎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከመንግስት፣ ከሲቪክ ማህበራትና ከመገናኛ ብዙሃን የሚጠበቀው ተነስቷል፡፡
ውይይቱ ዐበይት ባለ ድርሻ አካላት ያላቸውን ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም የምርጫ ስርዓትን በሚያስቃኝ ገለጻ የተጀመረ ሲሆን፥ የምርጫ ስርአት ላይም ውይይት ተካሂዷል፡፡
ዐበይት ዴሞክራሲያዊ ተቋማት መሠረታዊ ለውጥ ማካሄዳቸውን ተከትሎ የሚከናወነው ታሪካዊ ምርጫ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲ ጎዳና የምታደርገው ጉዞ ዓይነተኛ ማሳያ ይሆናል ተብሏል።
በውይይቱ ላይ ተሳታፊዎቹ አስፈላጊ መሠረታዊ ጉዳዮች ባልተሟሉበት ሁኔታ ምርጫ ለማድረግ መጣደፍን በተመለከተ ሃሳብ አንስተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ምቹ ሁኔታን መፍጠር፣ ከምርጫው አስቀድሞ የሕግ የበላይነትን ማስከበር እና የምርጫ ታዛቢዎችን ጨምሮ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚያገለግል የምርጫ ደንብ ማዘጋጀት አስፈላጊነት ላይም ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡
በተጨማሪም የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳታፊነት ማረጋገጥ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በተቀመጠው ህግ መሰረት ተሳታፊ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባም አውስተዋል፡፡
ቀጣዩ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ የሚሆንበትን መንገድ በተመለከተ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በአላዛር ታደለ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version