Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአሚሶም የ32ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የሰራዊት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መወያየቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሚሶም ሴክተር ሶስት የተሰማራው የ32ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የሰራዊት አባላት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡

ውይይቱን የመሩት የሴክተር ሶስት ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ዘውዱ ሰጥአርጌ እንደተናገሩት ፣ እዚህ ያለ መሪም ይሁን ተመሪ የጁንታው ቡድን በሰራዊቱ ላይ የፈፀመው የክህደት ተግባር በማውገዝ ኢትዮጵያን እና አህጉሩ የሰጠንን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በቁርጠኝነት መወጣት አለብን ብለዋል፡፡

በሰራዊቱ መካከል የጁንታው ቡድን ሊከፋፍል ሲጥር እንደነበረ በማንሳት ነገር ግን ሰራዊቱ የተሰጠውን ተልዕኮና የተላበሳቸውን እሴቶች ሳይሸረሸር ዛሬ ላይ ለደረሰበት የሞራልና የስነ ልቦና ጥንካሬ በቅተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሰራዊቱ አባላት በበኩላቸው ሰራዊቱ በተፈፀመበት ክህደት ሳይሸበር የጁንታውን ቡድን በመደምሰስ አከባቢውንና የትግራይን ህዝብ ነፃ ማውጣቱ የሚያኮራ ተግባር ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

Exit mobile version