የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ሆነው በተሾሙበት ቀን የግል ጠባቂዎችን ወደ ቢሮ እና መኖሪያ ቤት እንዳያስገቡ የደህንነት ቡድን ይከለክላቸው እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ

By Abrham Fekede

November 30, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ በ2010 ዓ.ም በአዲሱ አስተዳደር ሃላፊነት ሊኖራቸው በሚችሉ ሰዎች ላይ ህወሓት የክትትል ስርዓት ዘርግቶ ጫና ለመፍጠር ጥረት ሲያደርግ ነበር ብለዋል።

በወቅቱ ኢህአዴግ ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር ለእጩነት ከማቅረቡ በፊት ህወሓት በሚስጥር የእነሱን ፍላጎት የሚያሟላ ግለሰብ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ለማሾም ሲሰሩ እንደነበርም አውስተዋል፡፡

በ2010 ዓ.ም አዲሱ አስተዳደር ሁሉንም አሳታፊ የሚያደርግ የፖለቲካ ስርዓት ለመዘርጋት ቢነሳሳም የለውጥ ሀሳቡ በህወሓት ውድቅ ተደርጓል ሲሉም ተናግረዋል።

እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሾሙበት ቀን የግል ጠባቂዎቻቸውን ወደ ቢሮ እና መኖሪያ ቤት እንዳያስገቡ የደህንነት ቡድን ሲከለክላቸው እንደነበርም አስታውሰዋል።