Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምክር ቤቱ በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አንፀባራቂ ድል የተሰማውን ደስታ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አንፀባራቂ ድል የተሰማውን ደስታ ገለፀ።

ምክር ቤቱ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደሰ አላችሁ ብሏል።

የትግራይ ሕዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ላሳየው ሕዝባዊና ሃገራዊ ወገንተኝነትም አድናቆቱንና ምስጋናውን ገልጿል።

መከላከያ ሰራዊት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያሳየውን ቁርጠኝነትና ተጋድሎ በሃገሪቱ የህግ የበላይነትንና ፍትህን ለማረጋገጥ እጅግ ከፍተኛ ነውም ብሏል።

የከሀዲውን የጁንታ አባላት ለፍርድ ለማቅረብ በሚደረገው ቀጣይ እርምጃ ምክር ቤቱ በማንኛውም መልኩ ከሠራዊቱ ጎን እንደሚቆም ገልጾ ለሠራዊቱ ያለውን አጋርነት ዳግም ማረጋገጥ ይወዳልም ነው ያለው።

Exit mobile version