አዲስ አበባ ፣ ህዳር 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከህዳር 11 እስከ ህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ከ42 ሚሊየን 749 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጥይት፣ አደንዛዥ ዕጽ፣ ቡና፣ ግመሎች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ተይዘዋል፡፡
አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች፣ የመዋቢያ ቁሳቁሶችና መለዋወጫዎች፣ ሺሻ፣ ገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውንም ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዕቃዎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ በተለያዩ የጉሙሩክ ጣቢያዎች በጉሙሩክ ሰራተኞች፣ በህብረተሰብ ጥቆማ፣ በክልል ፖሊስ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በአድማ በታኝና በመከላከያ አባላት የጋራ ጥረት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከኮንትሮባንድ ዕቃዎች ማስተላለፍ ጋር ተያይዞ የተለያዩ አካላትና አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል፡፡