አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012(ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ በተገነቡ ቤቶች ላይ ከጥር 2 ጀምሮ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቋል፡፡
እርምጃው በተለይ በቅርብ ጊዚያት እየተስፋፋ የመጣውን የህገወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል ያለመ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡
እርምጃው በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 116 ወረዳዎች ላይ የሚወሰድ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስና የከተማዋ አጎራባች ወረዳዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡
በየወረዳው በህገወጥ መልኩ የተገነቡ ቤቶችን የመለየት ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በከተማዋ ባሉ ወረዳዎች ቦታዎቸን ለመያዝ በህገወጥ መልኩ እየታጠሩ እንደሆነና ከላስቲክ ቤቶች ጀምሮ የተለያዩ ህገወጥ ግንባታዎች እየተደረጉ እንደሆነ የተሰበሰቡት መረጃዎች ያሳዩ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡