የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የገጽ ለገጽ ትምህርት ህዳር 21 እንደሚጀመር ተገለጸ

By Abrham Fekede

November 27, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገጽ ለገጽ ትምህርት ህዳር 21 እና 28 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የመዲናዋ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በግል ትምህርት ቤቶቸ ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 21 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ከከተማ አስተዳደሩ ከትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ህዳር 28 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ትምህርት ቢሮው ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ህዳር 24 እና 25 እንደሚሰጥም አክለው ገልጸዋል።