አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የትራፊክ አደጋው በዛሬው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ ላይ መድረሱን ከሱሉልታ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከደብረ ታቦር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ከአዲስ አበባ ወደ አሊ ዶሮ ሲጓዝ ከነበረ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው።
በአደጋውም እስካሁን የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱም ታውቋል።