Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የግብፁ ፕሬዚዳንት  ነገ በደቡብ ሱዳን ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በነገው ዕለት በደቡብ ሱዳን ጉብኝት እንደሚያደርጉ  ተገለፀ።

ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በነገው ዕለት ጁባ የሚገቡ ሲሆን ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በተመለከተ እና ግንኙነቱን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉም ነው የተባለው።

እንዲሁም በቀጠናዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ  የደቡብ ሱዳን መንግስት አስታውቋል።

የአል ሲሲን ጉብኝት ታሪካዊ ነው ያለው የደቡብ ሱዳን መንግስት የጁባ ከተማ ነዋሪ ለፕሬዚዳንቱ አቀባበል እንዲያደርግም ጥሪ አቅርቧል።

Exit mobile version