ቢዝነስ

የኢትዮጵያ እና የኢንዶኔዥያ ቢዝነስ እና የንግድ ስብሰባ ተካሄደ

By Tibebu Kebede

November 27, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2020 የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና የኢንዶኔዥያ ቢዝነስ እና የንግድ ስብሰባ ተካሄዷል፡፡

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ከሃገራቱ የተውጣጡ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ተዋናዮች መሳተፋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ስብሰባው በሁለቱ ሃገራት ኤምባሲዎች እና በኢንዶኔዥያ ንግድ፣ ቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት ክለብ የተዘጋጀ ነው፡፡