አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012(ኤፍቢሲ) የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ለደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ኃላፊነቱ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ሆኖም የሶማሊያ ብሄራዊ የደህንነት ኤጀንሲ ጥቃቱ በሌላ ሀገር ታቅዶ የተፈፀመ መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡
ጥቃቱ በከተማዋ ደቡብ ምዕራብ ፍተሻ ጣቢያ የደረሰ ሲሆን በተሸከርካረ የተጠመደው ቦንብ ያደረሰው ጉዳት ከሁለት አመት ወዲህ በአፍሪካ ቀንዷ ሀገር በርካቶች ህይወታቸውን ያጡበት አደጋ ሆኗል፡፡
የአልቃይዳ ቃል አቀባይ ሼክ አሊ መሀመድ ራጌ ባስተላለፉት የድምጽ መልእክት እንደገለፁት የተፈፀመው ጥቃት የቱርካውያን ወታደሮችን ተሽከርካሪዎችን እና የአፖስቴት ታጣዎችን ኢላማ ያደረገ ነበር ብለዋል፡፡
የሶማሊያን የመንግስት አስተዳደር ለመቆጣጠር ላለፉት አስርት አመታት ትግል እያረገ የሚገኘው አልሸባብ በዋና ከተማ ሞቃዲሾ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ይፈፅማል፡፡
አልሻባብ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ላደረሰው ጥቃት ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን ይህ አካሄደም የሶማሊያን መንግስትና ደጋፊዎቹ ጋር በሚያደርገው ውጊያ አስፈላጊ ሆኖ ተወስዷል፡፡
ምንጭ፣ አልጀዚራ