Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህግ በማስከበር ላይ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊትናለአማራ ልዩ ሀይል የህክምና አገልግሎት ሲሠጡ የቆዩ የህክምና ባለሙያዎች አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍቢሲ)በትግራይ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው የህግ ማስከበር እርምጃ ወደ ግንባር ዘምተው የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
አቀባበል የተደረገላቸው በመጀመሪያው ዙር ወደስፍራው ያቀኑ የጤና ባለሙያዎችን ሲሆኑ÷የጤና ባለሙያዎቹ በሶስት ሳምንታት ቆይታቸው ከአብራሃጅራ እስከ ሁመራ ሆስፒታል ድረስ በየአካባቢው እየተንቀሳቀሱ ቁስለኞችን በብቃት ሲታደጉ የነበሩ ናቸውም ነው የተባለው።
ዛሬ ተልዕኳቸውን ጨርሰው ሲመጡ በባሕርዳር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአቀባበል ፕሮግራሙ ላይ የክልሉ ርዕስ መስተዳዳር አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወርቅ ሰሙ ማሞ እና የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ዶክተር መልካሙ አብቴ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ÷ጥቅምት 24 ቀን 2013 የህዋሃት ጁንታ ቡድን በመከላከያ ሰራዊቱ እና በአማራ ክልል ላይ ተኩስ የህክምና ግባአትናሌሎች ቁሳቁሶችን በማዘጋጀት የህክምና ባለሞያዎችን በሁሉም የጦርነት በተካሄደባቸው ቦታዎች ማስማራት መቻሉን ገልፀዋል።
በዚህም በሁሉም ግንባር የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የጤና ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን በጀግንነት እንደተወጡ ተናግረዋል።
በመሆኑም ባለሙያዎቹ ለሰጡት የህክምና ድጋፍ በክልሉ፣በፌደራል መንግስትና በመከላከያ ሰራዊት እውቅና እንደተሰጠው ገልጸዋል።
አቶ አገኘሁ አያይዘውም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የጤና ቢሮው የጤና ባለሞያዎችን መድቦ በመላኩ አመስግነዋል።
የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው÷ የህክምና አገልግሎት ስራ ከሚጠይቀው አንዱ ተግባር ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት መሆኑን አንስተዋል።
በዛሬው ዕለት 11የህክምና አባላት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን÷ ከ29 የህክምና አባላት ደግሞ አሁንም አውደውጊያው ቦታው ለመከላከያ ሠራዊት፥ለአማራ ልዩ ሀይልናሚሊሻ ህክምና በመስጠት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በናትናኤልጥጋቡ
Exit mobile version