የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሉን ግብርና ሜካናይዜሽን በቴክኖሎጅ ለማሳደግ ለሚሰሩ ባለሀብቶች ድጋፍ ይደረጋል

By Feven Bishaw

November 26, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል የግብርና ሜካናይዜሽን በቴክኖሎጅ ለማሳደግ ለሚሰሩ ባለሀብቶች ድጋፍ እንደሚደረግ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ÷ከወቅታዊ ስራዎች ጎን ለጎን የክልሉን የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ የክልሉ መንግሥት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ለዚህም አርሶ አደሮችን የግብርና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የሕብረት ሥራ ማኅበራትና ዩኒየኖችም በዘርፉ እንዲሳተፉ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

እንዲሁም የክልሉን ግብርና ሜካናይዜሽን ለማሳደግ ለሚፈልጉ ባለሀብቶችም ተገቢው ድጋፍ እንደሚደረግም ገልፀዋል፡፡