ዓለምአቀፋዊ ዜና

የቻይና-አፍሪካ የአየር ንብረት ትብብር ማዕከል በቤጂንግ ተከፈተ

By Meseret Awoke

November 26, 2020

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና እና አፍሪካ የአየር ንብረት ትብብር ማዕከል በቤጂንግ ተከፍቷል፡፡

ማዕከሉ ቻይና እና አፍሪካ በአየር ንብረት ለሚያደርጉት ትብብር ለሁሉም ክፍት፣ አካታችና በትብብር መንፈስ የተቃኘ ምቹ መደላድልን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም የአረንጓዴን ልማት ለማስፋፋት፣ የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን እና የአፍሪካ ህብረትን የ2063 አጀንዳን ለማሳካት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የትብብር መድረክን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ቻይና እና አፍሪካ የስነ ምህዳር እና የአየር ንብረት ለውጥን በመጠበቅ ረገድ የተሳካ የአየር ንብረት ትብብርን ማጠናከራቸው ይነገራል፡፡

የማዕከሉ መቋቋምም የትብብር ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር እና ለማሳደግ አዲስ መነሻ ይሆናልም ነው የተባለው፡፡

ማዕከሉ የአፍሪካ ሃገራት ለአካባቢ ጥበቃ እና ለዘላቂ ልማት ያላቸውን አቅም እንዲያሳድጉ እንደሚያግዝም ታምኖበታል፡፡

ምንጭ፡- ሲ.ጂ.ቲ.ኤን