Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት 24 ሰዓታት 518 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 556 ሰዎች ደግሞ ከቫይረስ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 283 የላቦራቶሪ ምርመራ 518 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 107 ሺህ 109 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 556 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 66 ሺህ 574 መድረሱ ነው የተነገረው።

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

Exit mobile version