አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያልተናገሩትን ንግግር እንደተናገሩት በመጥቀስ ለሰራው ሪፓርት ይቅርታ ጠየቀ።
ቢቢሲ ሞኒተሪንግ በትዊተር ገፁ ላይ ኢትዮጵያን በተመለከተ ትዊት ያደረግነውን የተሳሳተ ዘገባ አንስተናል ብሏል።
ጉዳዮ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለም እየገመገምን ነው ሲል ቢቢሲ ሞኒተሪንግ አስታውቋል።
ለተፈጠረው ስህተትም ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን ነው ያለው።
ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያልተናገሩትን ንግግር እንደተናገሩት በመጥቀስ ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱን የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ማስታወቁ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በመጥቀስ በትዊተር ገፁ ላይ ላሰፈረው ሀሰተኛ ፅሁፍ ተጠያቂ ይደረጋል ብሎ ነበር።
በትዊተር ገፁ ላይ የሰፈረውን ሀሰተኛ መረጃ ካሰራጨ አራት ሰዓታት በኋላ ሰርዞታል።