የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሌ እና አፋር ህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ ተካሄደ

By Tibebu Kebede

December 31, 2019

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ እና አፋር ህዝቦችን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ።

በውይይት መድረኩ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተሳትፈዋል።

መድረኩ “ህብረ-ብሄራዊ አንድነታችንን ለማጠናከር ውስጣዊ ችግሮቻችንን በምክክር እንፍታ!” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።

የውይይት መድረኩ የሶማሌ እና የአፋር ህዝቦችን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከርና አልፎ አልፎ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመቅረፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የምክክር መድረኩን የሰላም ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሃገር ሽማግሌዎች መማክርት ከጀስትስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሽፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።