የሀገር ውስጥ ዜና

የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ 30 ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይሰጣል

By Tibebu Kebede

November 24, 2020

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2012 ዓ.ም 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከታህሳስ 1 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ክልሎች በሚያወጡ መርሃ ግብር መሰረት እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሚሊየን ማቲዮስ በሰጡት መግለጫ በታህሳስ ወር ይሰጣል ተብሎ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወቅታዊ ጉዳይ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ገልፀዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው በመግለጫው ፈተናው ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚሰጥ በመሆኑ ተማሪዎች ዝግጅታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ለ45 ቀናት ከተወሰኑ ክልሎች ውጭ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን በመግለፅ አሁን ላይ የማካካሻ ትምህርቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በ2013 ዓ.ም ከ800 ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደሚወስዱ የተገለፀ ሲሆን ይህም ዝግጅቱ እንደቀጠለ እና ተማሪዎች እና ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉም ተጠይቋል።

በትዝታ ደሳለኝ